• Dr. Mulugeta Mengist

የክብሪት አፍራሽነት ሚና እና ስለ ባህል ጎጂነት

Updated: Nov 17, 2019ሰለሚያቃጥል አይደለም። ድሮ ገጠር ክብሪት ዉድ ነበር። እሳት አታጠፋም። አዳፍነህ ታድራለህ። ከባሰ ከጎረቤት ትጭራለህ።

ስንትና ስንት መንገድ እንኩቶ ለመብላት በሚል ተልካሻ ምክንያት እሳት በኩበት ይዘን ሄደናል።

እሳት አስጫሪ ማጣት ትልቅ መከራ ነዉ። ስለዚህ ጎረቤቱ ከጎረቤቱ ተሳስቦ በአንድነት ይኖራል። ሕግና መንግስት ሊያደርገዉ ከሚችለዉ በላይና በማይችሉበት ሁኔታ።

መጣልሃ ክብሪት! የእሳት መጫጫርን ግላዊ ጥቅም ተክቶ፤ የእሳት መጫጫርን ማህበራዊ አገልግሎት የማይተካ ክብሪት። የሕግና የመንግስትን ሚና እና ሃላፊነት የሚያበዛ።

አብሮ መነገድ እንኳን አለመድንም። ኩባንያ አቋቁመዉ ሶሰት አመት በጥሩ ትርፍ ከሰሩ በኋላ ያፈርሱታል። ለምን ቢባሉ፣ ራሳችንን እንቻል ብለን ነዉ ይሉሃል። የመደመር ህያዊ ጥቅም አልሰረፀብንም። አንድነት ከደካሞችና ለችግር ጊዜ ብቻ አይደለም። በጠንካሮች መካከል ያለ አንድነት በደካሞች መካከል ካለዉ ይልቃል።

ሌላዉ ነጥቤ፣ ጎጂ ባህል የሚባሉትን በጥንቃቄ መለየት ያስፈልጋል። የባህሎችን ወሳኝና ድብቅ አገልግሎቶች በዘመናዊነት ሰም እንዳናጣዉ። ባህሎች የትዉልዶችን ልምድና እውቀት አምቀዉ ይዘዋል። በእርግጥ ባህሎች የላቀ ፓለቲካ ሃይል ያለውን መደብ ጥቅም የሚያስከብሩ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ባህሎችን መመርመር ያስፈልጋል። በጥቅሉ ወይም በገለባው ከማሳጣታችን በፊት።

እሳት መጫጫር ጎጂ ባህል አይደለም። ክብሪት ግን ጎጂ ቴክኖሎጂ ሊሆን ይችላል። ፌስቡክስ?

የድሮ የገጠር ስርግ ትዝ አለኝ። ከብቶችህን ይዘህ ለሳምንት ከነቤተሰብህ ትከታለህ። ወደ ማይጨዉ ከዘመተዉ ጦር ተነጥሎ ኋላ የቀረ ዘማች ጦር ትመስላለህ። እንዲህ አይነት ባህል፤ ጎጂ ነዉ? ኤድመንድ በርክ ለአብዮተኛዉ ፈረንሳዊ ጓደኛዉ ሲጽፍ እንዲህ ይላል፤ “በዚህ የሰለጠነ ዘመን በልምዳችን እና በአይምሯችን ብቻ ሳይሆን በባህልም ጭምር ኑሯችንን እና ንግዳችንን የምንመራ መሆናችንን ስነግርህ በኩራት ነው። እነዚህን ባህሎች ከማፍረስ ይልቅ አጥብቀን እንይዛቸዋለን። አብዝተን እንጠብቃቸዋለን። ብዙ በቆዩ እና በአብዛኛዉ ሕዝብ ተቀባይነትን ባገኙ ቁጥር የበለጠ የሙጥኝ እንላቸዋለን። እያንዳንዱ ንግዱን እና ኑሮዉን በግል ልምዱ እና አይምሮዉ ብቻ እየተደገፈ እንዲመራ መፍቀድ ያስፈራናል። ምክንያቱም እያንዳንዱ ያለዉ ልምድና የአይምሮ ብቃት ዉስን ነዉ። ኑሮዉ እና ንግዱ የሚሻሻለዉ ከግል ልምዱና አይምሮአዊ ብቃቱ በተጨማሪ የዘመናትን እና የትዉልዶችን ልምድና ብቃት አከማችቶ ከያዘዉ ብሄራዊ የእዉቀት ባንክ ተጠቃሚ ሲሆን ነዉ። ለእናንተ ግን አንድን ነገር ለማፍረስ መቆየቱ ብቻ በቂ ምክንያት ነዉ። ያለፈዉ ትዉልድ የረባ ነገር ሰርቶ አላለፈም ብሎ የሚያምን ትዉልድ የቆየን ነገር ሁሉ እያፈረሰ፥ እርሱም ለሚሰራዉ ስራ ዘላቂነት/እድሜ ደንታ አይኖረዉም።”

  • @insights.of.jaaj

©2019 by fujaaj. All rights reserved.