• Dr. Mulugeta Mengist

አንድነት፣ አንድአይነትነትና፣ ብዝሃነት

Updated: Nov 17, 2019


አንድ አይነትነትና ብዝሃነት አብረዉ አይሄዱም።

አንድነትና አንድአይነትነት አብረዉ አይሄዱም። ምክንያቱም አንድአይነትነት ካለ፣ አንድነት የሚጨምረዉ ነገር የለም። እያንዳነዱ በነጠላዉ፣ ከጥቅሉ ጋር በአይነትም በመጠንም ተመሳሳይ ይሆናል። ስለዚህ አብሮነትም አይኖርም። ማህበራዊነትም አይኖርም። እያንዳንዱ ተናጥሎች ራሳቸዉን ችለዉ የሚኖሩ እግዝሃቤሮች ወይም አሜባዎች ናቸዉ። የሰዉነት ባህሪ አይደለም። ሰው ብቻዉን እንዲሆን ስለማይገባ በሚል ነዉ አጋር የተሰጠዉ። በራሱ ሙሉ እንዳይሆን።

የብዝሃነት መኖር፣ ለአንድነት፥ ማህበራዊነትና፥ ህያዉነት አሰፈላጊ ነዉ። ግን አንድነት በራሱ አይመጣም። ለላቀ አንድነት፥ ማህበራዊነትና፥ ህያዉነት ብዙ መስራት ይጠይቃል። ብዝሃነት ሲኖር፤ ጥቅሉ በአይነትም በመጠንም ከእያንዳንዱ ይለያል። የጥቅሉ አቅም፤ ከተናጠሉ አቅም ድምር ይበልጣል። አንድነት ህያዉነት የሚሆነዉ ለዚህ ነዉ። ጥቅሉ ይረቃል። ረቂቅ ነዉ ሲሉን፣ እኔ በዚህ መልኩ ነዉ የምረዳዉ።

ብዝሃነት ላይ አንድነት መገንባት የሚቻለዉ፤ በተናጥሎቹ መካከል ትብብር፣ ግብይት በማጠናከር ነዉ። ይህ ደግሞ እርስ በርሰ መግባባት ይጠይቃል። የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይጠይቃል። ራስን የመቻል ሳይሆን የበለጠ መተሳሰር ይጠይቃል። መተማመን ይጠይቃል። ከትምህርት፣ ህዝብ አሰተዳደር ሰርዓት፣ የፓለቲካ ስርዓት፣ ኤኮኖሚ፣ እስከ በጎአድራጎት ስርዓት ድረስ ያሉት ግብይትን፣ ትብብር፣ ትስስርን የሚያራምዱ ሳይሆን መነጠልን፣ ዜሮ ድምርን፣ የልዩነት ገደልን፣ አለመተማመን የሚፈጥሩ ናቸዉ። ይህ የሆነዉ መሪዎቻችን በታሪክ እግረሙቅ በመታሰራቸዉ ነዉ። እያንዳንዱን መመርመርና ማሰተካከል ያሰፈልጋል። እንደ ግለሰብ ልናደርገዉ የምንችለዉ ብዙ ነዉ። ለራሳችን ስንል።

መተማመንን፣ አኩልነትን፣ ግብይትን፣ ትብብርን፣ የጋራ ተጠቃሚነትና የጋራ ጫንቃን፣ መረዳዳትን፣ መግባባትን ሳንሰራ እነዚህን ይወክሉናል ባልነዉ ሰንደቅአላማ ጉንጭ ማልፋት ከንቱ ነዉ። አርማ የሌለዉ ሰንደቅ የሃገራችን አይደለም። ቢያንስ ሕገመንግስቱ እስካለ ድረስ።

አንድ ሰዉ አርማ የሌለዉን ሰንደቅ ቢያዉለበልብ፣ የኢትዮጲያን ሰንደቅ እያዉለበለበ አይደለም። እሱ እንኳን ነዉ ቢል፣ ስላለ አይሆንም። ድንጋይ ዳቦ ስላልነው ዳቦ አይሆንም። ከዚህ ዉጭ ግን ድርጊቱ ሕገመንግስቱን ይጥሳል፣ ያሰጠይቃል ማለት ባያሳዝን ኖሮ ያስቅ ነበር።

በዚህ አይነት የግብፅን ባንዲራ ባዉለበልብማ፣ ሕገመንግስቱን ጥሰሃል ማለት አይደለም፤ መንፈስቅዱስን ተሳድበሃል ልባል እችላለሁ።

ሀገራችን ዉስጥ ደግሞ ሕጋዊ የሀገራችን ሰንደቅ ያልሆነን በመስቀልና በማወለብለብ፣ መንግስትን የሚደርስበት የለም። ዛሬ እንኳን ስንት የኤርትራ ሰንደቅ ተዉለበለበ [የኤርትራዊ ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ በገቡበት ቀን የተጻፈ]።

Recent Posts

See All

የሽግግር መንግስት ህገመንግስታዊ ነው?

የዶር መሃሪ ታደለን ፅሁፍ አነበብሁት። https://meharitaddele.info/2020/05/the-limits-of-legal-solutions/ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚታወጀው ለመንግስት ተጨማሪ ስልጣን በመስጠትና መብቶችን በመገደብ በሽታውን ለመዋጋትና የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ ከሆኑ ብቻ ነው። መንግስ

  • @insights.of.jaaj

©2019 by fujaaj. All rights reserved.